የሪፎርም ሀሳብ ማሰባሰቢያ ውይይት

ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ወደ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መሸጋገሩን ምክንያት በማድረግና ተቋሙን ወደ ተሟላ ሪፎርም ለማስገባት ያመች ዘንድ የሪፎርም ሀሳብ ለማሰባሰብ ከጠቅላላ ሠራተኛዉ ጋር ዉይይት ተደርጓል፡፡

የኢንሰቲትዩቱ ፕሬዚዳንት አቶ እሱባለዉ መሠለ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ወደ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከተሸጋገረ በኋላ የሪፎርም ትግበራ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመዉና መነሻ ሠነዶች (Concept Papers) ተዘጋጅተዉ በተቋሙ ሥራ አመራር ቦርድ እና በማኔጅመንት ኮሚቴ ዉይይት ተደርጎ የሀሳብ ግብዓት በመዉሰድ ሰነዱን የማዳበር ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ዛሬም መነሻ ሠነዱን ለአጠቃላይ ሠራተኛዉ ማቅረብ ያስፈለገበት ዋናዉ ምክንያት በአንድ በኩል ተጨማሪ ሀሳብ ለማሰባሰብ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሠነዱን ከተቋሙ ዉጭ ካሉ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ዉይይት ከመደረጉ በፊት የተቋሙ ሠራተኛ ባለቤት ሆኖ ሪፎርሙን መምራት ስላለበት ነዉ ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አክለዉ አስረድተዋል፡፡

ሠነዶችን የምርምርና ስርፀት ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ቹቹ አለባቸዉ (ዶ.ር)፤ የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰብስበዉ አጥቃዉ (ዶ.ር) እና የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረቴ ዋለ በተከታታይ አቅርበዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሠራተኛዉ ሀሳብና አስተያየት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top