የካቲት 10/2018 ዓ.ም፣ ባህር ዳር
በአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለአመራሮችና ባለሙያዎች በGrant Proposal Writting ላይ ያተኮረ አስፈላጊ እና ውጤታማ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ።
……………………………………………………………………………………………………………………………
ስልጠናው የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የፕሮጀክት አቅም ለማጠናከር እና በውጭና በውስጥ የግራንት ድጋፎች ላይ የተሻለ ተወዳዳሪነት ለመፍጠር በተለይ ትኩረት አድርጎ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑ ታውቋል።
……………………………………………………………………………………………………………………………..
በሁለት ተከታታይ ቀናት ከየካቲት 09–10/2018 ዓ.ም የሚካሄደው ይህ ስልጠና፣ የግራንት ፕሮጀክቶች አይነቶች (Types of Public Grants)፣ አሳማኝ የግራንት አጻፃፍ (Persuasive Grant Writting)፣ የፕሮጀክት የማቀድ ሂደት (Creating Planning Process) እና የግራንት ፕሮፖዛል ክፍሎች (Grant Proposal Writting Sections) በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይ በጥልቀት ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል።
……………………………………………………………………………………………………………………………..
ተሳታፊዎች ውጤታማ እና ተወዳዳሪ የግራንት ፕሮጀክቶችን ለማዘጋጀት የሚያግዙ ተግባራዊ ክህሎቶችና ዘመናዊ መንገዶችን እንደተማሩ ተገልጿል።
ስልጠናው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ገበየሁ መንገሻ የተሰጠ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ዳይሬክተሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለሙያዎች በስፋት ተሳትፈዋል።
……………………………………………………………………………………………………………………………..
ዩኒቨርሲቲው እንደገለጸው፣ እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎች በምርምር፣ በልማት ፕሮጀክቶች እና በኢንስቲትዩሽናል አቅም ግንባታ ዘርፍ የሚያሳድጉ ሲሆኑ፣ የግራንት ፈንዶችን በብቃት ለመሳብ የሚያስችሉ መሠረታዊ መድረኮች ናቸው።
በመሆኑም ይህ ስልጠና የዩኒቨርሲቲው የምርምር ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና ከተለያዩ የፋይናንስ ድጋፍ ምንጮች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።