ከ1 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ሠልጣኞች ሥልጠና ተሠጥቷል።
ከዚህ ቀደም ሥልጠናዎች የሚሰጡት በተቋማት ጥያቄ ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በኋላ ግን አጫጭር ሥልጠናዎች የሚሰጡበት ሥርዓተ ትምህርት መቀረጹን ጠቁመዋል። 16 የማሠልጠኛ ሞጂሎችም ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
በዩኒቨርስቲው ሦሥት ምርምሮች ማጠናቀቅ ተችሏል ያሉት አቶ እሱባለው ችግር ፈቺ ምርምሮችን በመለየትም ወደፊት በስፋት ይሠራበታል ነው ያሉት።
የሴት ሠራተኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ሥልጠናዎችም ተሰጥቷል።
ኢንስቲትዩቱ ወደ “አማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሸጋገር የክልሉ መንግሥት በወሰነው መሠረት ወደ ሥራ ተገብቷል ነው ያሉት። በቀጣይ ቀናትም በይፋ ይገለጻል ብለዋል
የስቴት ዩኒቨርስቲው ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሠራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለአቅመ ደካሞች ቤት ሠርቷል፤ በችግር ውስጥ ያሉ ሕጻናትንም እየደገፈ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የዩኒቨርስቲው ዲጂታላይዜሽንን ለማሳደግ እየሠራ ነው ያሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት እሱባለው መሠለ አሠራርን ከወረቀት ንክኪ ነጻ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናዎኑ ነው ብለዋል። ይበልጥም መዘመን እንደሚገባው ነው የተናገሩት።
በዩኒቨርስቲው የተገልጋዮችን እርካታ ለማወቅ በተሠራው ጥናት የእርካታ ከፍታው 66 በመቶ ላይ ይገኛል ብለዋል። ይህም በቀጣይ በትኩረት ለመሥራት አመላካች እንደኾነም አስረድተዋ
በሣይበር ደህንነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ
ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም ለአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ሠራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስቴት ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አቶ እሱባለው መሠለ እንደገለፁት የቴክኖሎጅ መሠረተ ልማት እና መሠረታዊ የሣይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ስልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ስልጠናው በስቴት ዩኒቨርስቲው ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ፀሀየ አስረስ ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናውም ሁሉም የስቴት ዩኒቨርስቲው አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡